የማእከሉ አደረጃጀት

ማዕከሉን የማቋቋም ሀሳብ ያመነጩት የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባለሙያዎች ሲሆኑ በ2001 ዓ.ም.  በኦሮሞ ባህል ጥናት እና እድገት ላይ ያለዉን ክፍተት ለመቅረፍ በማሰብ ነዉ፡፡ይህ መነሻ ሀሳብ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቀርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ ክልሉ ለማዕከሉ ግንባታ ስራ የሚዉል በጀት መድቦ ግንባታ እንዲጀመር ተደረገ፡፡ የማዕከሉ ግንባታ የተጀመረዉ በ2001 ሲሆን በ 2007 ዓ.ም. ማዕከሉ ተመርቆ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ማዕከሉ እንደ አንድ የመንግስት ተቋም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ደንብ ቁጥር 167/2006 ዓ.ም. እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ማዕከሉ 10 የተለያዩ ብሎኮች ያሉት ሲሆን የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች አሉት፡፡እነኚህ ክፍሎች እንደ ቤተመፃሕፍት፡የጥናትና ምርምር
ክፍሎች፡ ሙዝዬም፤ የአርት ስልጠና ክፍል ፡የስብሰባ አዳራሽ እና ወዘተ ሆነው ያገለግላሉ፡፡

ማዕከሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

                            1.      በባህል፤ ቋንቋ፤ ታሪክ፤ ላይ ጥናት እና ምርምር ማድረግ

                            2.     ሙዚዬም በማደራጀት ለህዝብ እይታ ማቅረብ

                             3.     በአርት እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠት

                             4.     ቤተመፃሕፍት አደራጅቶ ለተገልጋዮች መረጃ ማቅረብ