የኦሮሞ ባህል ማዕከል የሥራ ድርሻ እና ሥልጣን

የኦሮሞ ባህል ማዕከል በአዋጅ ቁጥር 167/2006 የተሰጠዉን የሥራ ድርሻ እና ሥልጣን መሰረት በማድረግ የኦሮሞን ባህል ፤ታሪክ፤ ቋንቋ፤አርትን በማጥናት እንዲሁም የኦሮሞ ሙዚዬም ደረጃዉን የጠበቀ እንዲሆንና  ለህዝቡ ሊጠቅም በሚችልበት መንገድ እንዲሰራ  ከላይ በተጠቀሰዉ አዋጅ ለማዕከሉ የስራ ድርሻ እና ሥልጣን ተሰቶታል፡፡ እነዚህም

1.  የኦሮሞን ቋንቋ፤ታሪክ፤አርት በከፍተኛ ደረጃ ያጠናል፤ በሌላ ክፍልም ያስጠናል፤ የጥናት ዉጤቶችን በማሳተም ለሚመለከተዉ አካል ያከፋፍላል በስርዓተ ትምህርት  ዉስጥ እንዲካተቱ ቅድመ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ፤ለሚጠናዉ ጥናትም ድጋፍ ይሰጣል፡፡

2.     አፋን ኦሮሞን በተመለከተ የፊደል አፃፃፍ ግድፈትን፤ በቋንቋዉ አጠቃቀም ላይ ጥናት እና ምርምር ያካሄዳል ፤ሥራ ላይ መዋሉንም ይቆጣጠራል፡፡

3.     የቋንቋዉን መደበኛ ኮሚቴ በማዕከላዊነት ያካሄዳል ስያሜ ያገኙትን ቃላቶች ለሚመለከተዉ አካል ያደርሳል፤ ሥራ ላይ መዋሉንም ይቆጣጠራል፡፡

4.     በክልል ደረጃ የእዉቀት ማዕከል የሆነ ቤተ መፃህፍትን ያደራጃል፤ ፈጣን እና ዘመናዊ የሆነ መረጃ ህዝቡጋ እንዲደርስ ይሰራል፡፡

5.     በክልል ደረጃ ታሪካዊ የሆኑትን መዛግብት ይሰበስባል፤ ይመዘግባል ለጥናት እና ምርምር ፋይዳ እንዲዉሉ ያደርጋል፡፡

6.     ወደ ማዕከሉ ያልመጡ መዛግብቶችን ባሉበት ቦታ እንዲጠበቁ ክትትል ያደርጋል ፤በሥራ ቦታዎች ዉስጥ ተገቢዉን የስራ ጊዜያቸዉን የጨረሱትን መዛግብት ወደ ማዕከሉ በማምጣት እንክብካቤ በማድረግ ለተገልጋይ ተደራሽ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡

7. ለአፋን ኦሮሞ ዕድገት በታሪክ እና በባህል ላይ የተፃፉ መፃህፍትን ይሰበስባል ያደራጃል እንዲሁም አንባቢያን እዲጠቀሙት ያደርጋል፡፡

8.     በኦሮሞ ታሪክ፤ባህል፤ ቋንቋ ላይ በማንኛዉም ቋንቋ ተፅፈዉ የታተሙ እና ያልታተሙ ጽሁፎችን ይሰበስባል እንደ አስፈላጊነቱ የተመረጡትን ያሳትማል፤ በግዥም ሆነ በነፃ ያከፋፍላል እንዲሁም በቤተመፅሀፍት  ዉስጥ ለአንባቢያን ጥቅም እንዲዉል ያደርጋል፡፡

9.  በክልል ደረጃ ትያትር ቤት በማዘጋጀት ትያትር፤ ፊልም፤ ሙዚቃ የመሳሰሉትን በማዘጋጀት አገልግሎት ይሰጣል እንዲሰጥም ያደርጋል፡፡

10.   ከትያትር ሙያ ጋር የተያያዙ የረጅም እና የአጭር ጊዜ ስልጠና ይሰጣል እንደ አስፈላጊነቱ የማሰልጠኛ ተቋም ይገነባል፡፡

11. ደረጃዉን የጠበቀ የኦሮሞ ሙዚዬም  ሳይንሳዊ በሆነ ሁኔታ ያደራጃል፤ የማህበረሰቡን ታሪክ እና ባህል የሚገልጹ የባህል እቃዎችን ይሰበስባል፤ ይንከባከባል፤ ይጠብቃል ለህዝብ ክፍት በማድረግ ያሳያል፡፡

12.  ለጥናት እና ምርምር የሚሆኑ ባህላዊ እቃዎችን በመለየት ያስቀምጣል እንዲሁም ለሙዚዬሙ የሚሆኑ ባህላዊ እቃዎችን በግዥእና በስጦታ መልክ የሚሰጡትን ይሰበስባል፡፡

13.   የተለያዩ አዉደርይኦችን በማዘጋጀት አገልግሎት ይሰጣል፡፡

14.   የማዕከሉን አላማ ለሚደግፉ ማህበራት፤ ግለሰቦች ድጋፍ እና ትብብር ያደርጋል፡፡

15.   ከአገልግሎት የሚገኘዉን ገቢ ይሰበስባል፤ በሒሳብ ደንብ መሰረት  ስራ ላይ ያዉላል፡፡

16.  ማዕከሉን በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የመከሰስም ሆነ የመክሰስ መብት አለዉ፡፡

17.  የማዕከሉን የዉስጥ ገቢ ማሳደግ ከሚችሉት ጋር በመሆን የዉስጥ ገቢ ማመንጨት ለሚችሉት አገልግሎት ይሰጣል፡፡