ዜና

2012 .. ኢሬቻ በዓል በፊንፊኔና በሆራ ሀርሰዲ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ ተካሄደ፡፡

የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ኤግዚብሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡

ዝርዝር ዜና

v 2012 . የኢሬቻ በዓል በሆራ ፊንፊኔና በሆራ ሀርሰዲ ቢሾፍቱ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል፡፡ የሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ 150 ዓመታት ከተቋረጠ በኃላ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩ ሁኔታ መከበሩን የበዓሉ አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡

የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በፊንፊኔ መስከረም 24 በቢሾፍቱ መስከረም 25 በታላቅ ዝግጅትና ድምቀት የተከበረ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችም ተሳትፈውበታል፡፡

v ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ ተካሄደ፡፡ 2012 . የኢሬቻ በዓል ታሪካዊና ልዩ ከመሆኑ የተነሣ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡ ከነዚህ ዝግጅቶች አንዱ ታላቁ የኢሬቻ ሩጫ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ኢሬቻ ግሬት ራን በሚል መስከረም 11 ቀን 2012 . የተካሄደ ሲሆን 60000 ሰዎች በላይ ተሳትፈውበት 1 እስከ 3 ለወጡ አሸናፊዎችም የብርና ሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

v የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ ኤግዚብሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡ 2012 . በሆራ ፊንፊኔ የተከበረውን የኢሬቻ በዓል ምክንያት በማድረግ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ኤግዚብሽንና ባዛር ተከፍቷል፡፡ በዚህ ባዛር ላይ የተለያዩ የኦሮሞ ባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች፤ የተለያዩ የባህል ምግቦችና መጠጦች፤ መፃህፍትና ሌሎች ባህላዊ ነገሮች ለእይታና ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡ በተጨማሪም የኢሬቻን በዓል ምክንያት በማድረግ የገዳ ፌስቲቫልም በኦሮሞ ባህል ማዕከልና በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡

v በኦሮሞ ባህል ማዕከል ውስጥ የሚገኘው ገዳ ኢንተርናሽናል ካፌም በዓሉን በማስመልከት 4200 ሜትር ርዝመት ያለው ጩኮ/ሚጪራ/ ባህላዊ ምግብ ማዘጋጀቱ ተገልጻጿል፡፡ ይህ ባህላዊ ምግብ ከገብስ ዱቄት፤ ቅቤና የተለያዩ ቅመማ ቅመሞች የሚሰራ ሲሆን ውሃ ሳይገባበት በቅቤ ብቻ ታሽቶ የሚሰራ የኦሮሞ ባህላዊና ተወዳጅ ምግብ ነው፡፡ ይህንን ባህላዊ ምግብ በዚህ ርዝመት ሰርተው በዓለም ዕውቅ መዝገብ (ጊነስ ቡክ) ለማስመዝገብ ማቀዳቸውን የካፌው ባለቤት ገልጸዋል፡፡

v ከዚህም ሌላ የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በተለያዩ የሙዚቃ ኮንሰርቶችና ዝግጅቶች የተከበረ መሆኑንና በዓሉም በታላቅ ድምቀትና በሰላም መጠናቀቁን የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ገልጿል፡፡