የመስሪያ ቤቱ ድጋፍ ሰጪ ክፍሎች
በኦሮሞ ባህል ማዕከል ለሚሰሩት ስራዎች ድጋፍ
ለመስጠት እና የሚሰራዉ ስራ በተቀላጠፈ መንገድ እንዲከናወን ድጋፍና ክትትል የሚሰጡ ክፍሎች አሉ፡፡እነሱም
1. እቅድ ክፍል
2. የሰዉ ሐይል
3. ፋይናንስና
4. ኦዲት ናቸዉ፡፡
የሰዉ ኃይል
·
በማዕከሉ ውስጥ በተለያዩ የስራ ድርሻዎች የሚሳተፉ 138 ሠራተኞች አሉ፡፡ ከነዚህ ዉስጥ 86 ወንዶች ሲሆኑ
52 ሴቶች ናቸዉ፡፡
·
የሰው ኃይል ዳይሬከቶሬት የራሱ ዕቅድ በማዘጋጀት የሚሰራ ሲሆን ያደረጃል፣ ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣ ይወስናል፤ ይቆጣጠራል፣ የስራ አፈጻጸምን ይገመግማል፣ ክፍተቶችን ይለያል ፡፡
·
ማዕከሉ በሚፈልገዉ ክፍት የስራ ቦታ
ላይ የሰዉ ኃይል ይቀጥራል፤ ስለ መንግሥት መመሪያዎችና ደንቦች እንዲሁም ተቋሙ ስለተቋቋመበትና ስለሚጠበቅበት ውጤት እንዲሁም ስለ
መሥሪያ ቤቱ ልዩ ልዩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊነት የማስተዋወቂያና የአቅም ግምባታ ስልጠና (Inducation) እንዲሰጥ በማድረግ ወደ
ሥራ እንዲሰማሩ ያደርጋል፣
·
በመንግሥት ሠራተኞች መመሪያዎችና ደንቦች
መሠረት መካከለኛ አደረጃጀት ላለው ተቋም ልዩ ልዩ የቅጥር፣ የደረጃ
ዕድገት፣ ዝውውር፣ የድሲፕሊን፣ የቅሬታ ማስተናገጃና እንዲሁም ሌሎች አግባብነት ያላቸው ኮሚቴዎች እንዲቋቋሙና ተግባራዊ እንዲሆኑ
ይከታተላል፣
የእቅድ ክፍል
·
በማዕከሉ የሚገኘዉ የዕቅድ ክፍል የማዕከሉን
የተለያዩ የስራ ቡድኖችን ስራ ያቅዳል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ውሳኔ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል፣ግብረ መልስ ይሰጣል፡፡
·
የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለመሥሪያ ቤቱ
የበላይ ኃላፊ ያቀርባል፡፡
·
የእቅድና በጀት ዝግጅትና ሪፖርት፣ የግምገማና ግብረ መልስ ሥራዎች ውጤታማና ቀልጣፋ እንዲሆኑ የአሠራር ስርዓቶችን
ይዘረጋል፣
የፋይናንስ ክፍል
·
በማዕከሉ የሚገኘዉ የፋይናንስ ክፍል ከተቋሙ ስትራቴጂክ እቅድ በመነሳት የአጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ
እቅድ ያወጣል፣ ሲፈቀድም አፈጻጸሙን ይቆጣጠራል፡፡
·
አስፈላጊ የሆኑ የስራ መገልገያ መሳሪያዎችና የሰው ሃይል እንዲሟላ ያደርጋል፡፡
·
የፋይናንስ፤ የበጀትና የሂሳብ አያያዝ
ተግባራትን በሂሳብ አሠራር መርሆችና ደንቦች መሠረት መከናወናቸውን ያረጋግጣል፤
·
በንብረት አያያዝና ክምችት ላይ የኦዲት
ሪፖርቶችን ተግባራዊነት ይከታተላል፤ የበጀት፤ የግዢ፤ የፋይናንስና የንብረት አፈፃፀምና የስራ ፍሰት፤ የግንኙነት ሰንሰለትና የቁጥጥር
ስርዓትን ይዘረጋል፡፡
የኦዲት ክፍል
·
ከመ/ቤቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ በመነሳት የዳይሬክቶሬቱን ፐርፎርማንስና ፋይናንሽያል ሥራዎች ያቅዳል፣
ይመራል፣በሥሩ ለሚገኙ ቡድኖች ሥራዎችን ያከፋፍላል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ያስተባብራል፣
·
የተቋሙ የክፍያ አፈጻጸም፣ የሂሳብ አያያዝ፣
የንብረት አያያዝና አጠቃቀም፣ የንብረትና የአገልግሎት ግዢ መንግስት ባወጣው ደንብና መመሪያ መሰረት መከናወኑን ማረጋገጥ፣
·
ተቋሙ የሚመራባቸው አግባብነት ያላቸው
አዋጆች፣ ደንቦችና መመሪያዎች በትክክል ተፈጻሚ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣