ቤተ መጽሓፍትና ቤተ መዛግብት

ማዕከሉ በኦሮሚያ ደረጃ አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ መፃሕፍት ያለው ሲሆን ለአንባቢዎችና ጥናት ለሚያደርጉ ሰዎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ፃሕፍት፤ ጥናቶችና ህትመቶችን አሰባስቦ በማደራጀት ለተጠቃሚዎች እያቀረበ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም አዳዲስ መረጃዎችን ለአንባቢያን ለማድረስ ኢንተርኔት በመዘርጋት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ 

ቤተ – መዛግብት

የኦሮሞ ባህል ማዕከል የራሱ የሆነ መዛግብት ያለዉ ስሆን በዚህ ክፍል ዉስጥ ሀገራዊ ቅርስነት ያላቸዉን ልዩልዩ ፅሁፎች በማሰባሰብ እና በማደራጀት ለአጥኝዎች እንድሁም መረጃዉን  ለሚፈልጉ ሰዎች አመቻችቶ በማኖር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡