የኦሮሞ ባህል ማዕከል

የማዕከሉ አደረጃጀት


ማዕከሉን የማቋቋም ሀሳብ ያመነጩት የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባለሙያዎች ሲሆኑ በ2001 ዓ.ም.  በኦሮሞ ባህል ጥናት እና እድገት ላይ ያለዉን ክፍተት ለመቅረፍ በማሰብ ነዉ፡፡ይህ መነሻ ሀሳብ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቀርቦ ተቀባይነት በማግኘቱ ክልሉ ለማዕከሉ ግንባታ ስራ የሚዉል በጀት መድቦ ግንባታ እንዲጀመር ተደረገ፡፡ የማዕከሉ ግንባታ የተጀመረዉ በ2001 ሲሆን በ 2007 ዓ.ም. ማዕከሉ ተመርቆ ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ማዕከሉ እንደ አንድ የመንግስት ተቋም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ደንብ ቁጥር 167/2006 ዓ.ም. እንዲቋቋም ተደርጓል፡፡ ማዕከሉ 10 የተለያዩ ብሎኮች ያሉት ሲሆን የተለያዩ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎች አሉት፡፡እነኚህ ክፍሎች እንደ ቤተመፃሕፍት፡የጥናትና ምርምር
ክፍሎች፡ ሙዝዬም፤ የአርት ስልጠና ክፍል ፡የስብሰባ አዳራሽ እና ወዘተ ሆነው ያገለግላሉ፡፡

ማዕከሉ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከተሉትን ያካትታል፡፡

                            1.      በባህል፤ ቋንቋ፤ ታሪክ፤ ላይ ጥናት እና ምርምር ማድረግ

                            2.     ሙዚዬም በማደራጀት ለህዝብ እይታ ማቅረብ

                             3.     በአርት እና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ስልጠና መስጠት

                             4.     ቤተመፃሕፍት አደራጅቶ ለተገልጋዮች መረጃ ማቅረ

ሕዝብና ባህል

ኢትዮጵያ ካላት ብሄር ብሄረሰቦች መካከል ኦሮሞ አንዱ እና ዋነኛዉ ነዉ፡፡ ከአገሪቱ የቆዳ ስፋት አንፃር  ሰፊዉን ቦታ የያዘ እና አገሪቱ ካላት የሰዉ ቁጥር ዉስጥ ከፍተኛዉን ይዞ የሚገኝ ብሄር ነዉ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ የሚናገረዉ ቋንቋ አፋን ኦሮሞ ሲሆን ይህም ከኩሽ ነገድ ዉስጥ የሚመደብ ሆኖ አፍሮ ኤዥያዊ የሆነ ቋንቋ ቤተሰብ ነዉ፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ በአንድ አምላክ የሚያምን ሲሆን የሚተዳደረዉ የራሱ በሆነዉ በገዳ ስርአት ነዉ፡፡ ይህም በስርዓቱ ዉስጥ ተመርጦ የሚመራዉ ሰው በብዙ ቅድመ ሁኔታዎች ዉስጥ አልፎ ለ8 ዓመታት ህዝቡን ካገለገለ በኃላ ስልጣኑን  ለሚቀጥለዉ አመራር በሰላም ያስረክባል፡፡

የኦሮሞ ሕዝብ ከሌላዉ ማህበረሰብ እና ከራሱም ጋር ሲኖር የራሱ የሆነ ባህላዊ ተምሳሌት፤ ህል፤ ወግ፤ ልማድ፤ ያለዉ ብሔር ነዉ፡፡ ለምሳሌ በገዳ ስርዓት ውስጥ የተለያዩ ማህበራዊ ተቋማት ያሉ ሲሆን ታሪክ እና ባህሉን በስፋት ይዳስሳሉ፡፡ የገዳ ሥርዓት የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚያስተናግዱ እና አያሌ የግጭት አፈታት ጥበቦችን በዉስጣቸዉ ያካተቱ ተቋማት አሉት፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ሲንቄ፤ጉድፈቻ፤ሞጋሳ፤አቴቴ፤ጉማ፤ከለቻ፤ሽምግልና (እርቅ) የመሳሰሉትን ተቋማት በአስተዳደሩ ዉስጥ ሲገለገልባቸዉ ቆይቷል፤ በመገልገል ላይም ይገኛል፡፡ የእነዚህን ተቋማት ዝርዝርና በገዳ ሥርዓት ዉስጥ ያላቸዉን ሚና በሌላ ጊዜ በሰፊዉ ማየት ይቻላል፡፡

                                                                   ባህልና ቅርስ

የገዳ ስርዓት  አስተዳደር በርካታ  አደረጃጀቶችን ወይም ተማትን በዉስጡ ያካተተ ሰፊ እና ረቂቅ የሆነ ስርዓት ነዉ፡፡ገዳ ሁለንተናዊ የማህበረሰብ ዕድገት ጋር ተያያዥነት ያለዉ ሥርዓት ሲሆን የማህበረሰቡን አጠቃላይ የተፈጥሮ መስተጋብር በማካተት ለአጠቃላይ እድገት እና እንክብካቤ የሚተጋ  ነዉ፡፡ ይህም ማለት የገዳ ስርዓት ስለ ሰዉ ልጅ አስተዳደር ፤ ስለዕፅዋት ፤ስለእንስሳት ፤ ስለሚኖርባት ምድር ህግና ደንብ ያለዉ መሆኑ በጥናትና ምርምር ታዉቆ በአለም ቅርስነት በ UNSCO  ተመዝግቧል::

የገዳ ሥርዓትና ትላልቅ ተ

ከገዳ ሥርዓት ዉስጥ ከተዋቀሩት sማት መካከል የተወሰኑት ርስ በርስ ግጭት ውስጥ የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የሚጠቀሙ ናቸዉ፡፡ ይህም አንድን በግጭት የተጎዳ ህብረተሰብ መልሶ ወደ ሰላም ለማምጣትና የተረጋጋ ሕይወት ይመሩ ዘንድ የአስታራቂነት ድርሻ አላቸዉ እነዚህ ሠላምና እርቅን የሚያወርዱ ማት የጉማ፤የከለቻ፤ጫጩ፤ሲንቄ፤ ቦኩ፤ ሽምግልና እና  የመሳሰሉት ናቸዉ ፡፡ ከነዚህም መካከል የሲንቄ  ደንብና ሥርዓትን  እንመልከት፡፡

ሲንቄ

ሲንቄ ግጭቶች አለመግባባቶችን ባሉበት ሥፍራዎች እደ ቦኩ ሁሉ ያላንዳች ሥጋት በጠቡ መካከል በመግባት እኩይ ድርጊቱን እንዳይፈፀም ተገን በመሆን ግጭቱን

የኦሮሞ ጥናት ማዕከል


የኦሮሞ ጥናት ማዕከል በኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የተጀመሩትን የጥናት ፕሮጀክቶችን አስቀጥሏል፡፡ በዚህ መሰረት የተለያዩ መጽሐፍት  ዘጋጀ ሆን ለህብረሰቡም  ተራሽ አድርጓል፡፡

 

የኦሮሞ ሙዚየም


የኦሮሞ ባህል ማዕከል ተመርቆ ስራ  ከጀመረ ማግስት ጀምሮ ለአገር ዉስጥ እና ለዉጭ ጎብኝዎች በሚመች መልኩ ከኦሮሞ አስር (10) የባህል ዞኖች የተሰባሰቡትን የኦሮሞ ባህል መገለጫ የሆኑ ቅርሶችን በማሰባሰብ እና በማድራጀት  ለጎብኝዎች  ማለትም ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ ዩንቨርስቲ ተማሪች ፤ ለአገር ዉስጥ ጎብኝዎች ፤ለዉጭ ጎች ፤ለተመራማዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ቤተ መጽሓፍትና ቤተ መዛግብት


ማዕከሉ ለአንባቢዎችና ጥናት ለሚያደርጉ ሰዎች አገልግሎት የሚሰጥ ቤተ መጽሐፍት አለው፡፡ቤተ መጽሐፍቱ የቤተ መዛግብት ክፍልም አለው፡፡

አርትና ትያትር

የትያትር አዳራሽ ስራውን የጀመረ ሲሆን የሙዚቃና ትያትር ፕሮግራሞችን ማስተናገድ ችሏል፡፡ ለመንግስት፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማትና ለሲቪልማህበራት አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ እንደዚሁም ለአርትስቶችና ለኦሮሞ ደራሲያን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

ያግጙን

  • ኣዲሲ ኣበባ ሲተዲየም ባቡሪ ጣቢያ ፊትለፊት

  • gedafekadu@gmail.com
  • (+251) 115 580 262
  • (+251) 115 580 262