የገዳ ሥርዓትና ትላልቅ ተቋማት

 


ከገዳ ሥርዓት ዉስጥ ከተዋቀሩት ማት መካከል የተወሰኑት ርስ በርስ ግጭት ውስጥ የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የሚጠቀሙ ናቸዉ፡፡ ይህም አንድን በግጭት የተጎዳ ህብረተሰብ መልሶ ወደ ሰላም ለማምጣትና የተረጋጋ ሕይወት ይመሩ ዘንድ የአስታራቂነት ድርሻ አላቸዉ እነዚህ ሠላምና እርቅን የሚያወርዱ ማት የጉማ፤የከለቻ፤ጫጩ፤ሲንቄ፤ ቦኩ፤ ሽምግልና፤  የመሳሰሉት ናቸዉ ፡፡ ከነዚህም መካከል እስት የሲንቄ s ደንብና ሥርዓት እንመልከት፡፡

 

ሲንቄ

ሲንቄ ግጭቶች አለመግባባቶች ባሉበት
ሥፍራዎች እንደ ቦኩ ሁሉ ያላንዳች ሥጋት በጠቡ መካከል በመግባት እኩይ ድርጊት እንዳይፈፀም ተገን በመሆን ግጭቱ እንዲበርድ ወይምእንዲቆም ያደርጋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ሲንቄ ሰላምና መረጋጋት ይሰፍን ዘንድ ሴቶችን በማደራጀት በኩል ትልቅ ሥፍራ አለዉ፡፡

ከሽማግሌዎች ባሻገር የተገዳደሉት ክፍሎች ካሉ ሴቶች ሲንቄአቸዉን ይዘዉ ወደ አንድ ታዋቂ መድረክ በመሰባሰብ ለእርቀ ሰላሙ መዉረድ ልመናቸዉን ያቀርባሉ፡፡ ʿታረቀን መረባʾ በማለትበዜማ መልክ ይለምናሉ ፤ምህረቱንና እርቁን የተጠየቁት ወገኖች ይሁንታቸዉን እስኪያሳዉቁ ድረስ ልመናዉ የሚቀጥል ሲሆን ወደቤት መመለስም የማይቻል ነገር ነዉ፡፡ ሴቶች ሲንቄአቸዉን ይዘዉ ከቤት ወጡ ማለት መላ ቤተሰብ ተራበ ማለት ነዉ፡፡ ይኸዉም ጥጆች ከጥገቶች አይገናኙም፤ ለሕፃናት ምግብ የሚያዘጋጅ አይኖርም፤ እንዲሁም ለቤተሰብ ምግብ የሚያቀርብና ወደ ሥራ የሚያሠማራ ሀይል ጠፋ ማለት ነዉ፡፡ 

ስለዚህየበለጠ ጥፋት እንዳይደርስ ሲሉ ሽማግሌዎችና አዋቂች የቦኩና የአባ ገዳ አመራሮች በዚያ መድረክ ላይ በመገኘት በአጋርነት ከሴቶች ጎን ይቆማሉ፡፡ የችግሩን መንሰኤ በማጥናት ሁለት ተፋላሚዎች ወደ ሠላም መድረክ እንዲመጡ ይደረጋል፡፡

በዉሳኔዉም የበደለዉ ወገን እዲክስ ተበዳዩም ወገን ካሳ እንዲቀበልይደረጋል፡፡ በዚህ መልኩ ሲንቄ የሠላምና የእርቅ ተቋም በመሆን በሕብረተሰቡ ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋፆኦ ሲያደርግ የቆየ ነዉ፡፡ ምንጭ (በገዳ ሥርዓት የቱለማ ኦሮሞ ፖለቲካ
2000)