የገዳ ሥርዓትና ትላልቅ ተቋማት
ከገዳ ሥርዓት ዉስጥ ከተዋቀሩት ተsማት መካከል የተወሰኑት በእርስ በርስ ግጭት ውስጥ የተፈጠሩትን ችግሮች ለመፍታት የሚጠቀሙ ናቸዉ፡፡ ይህም አንድን በግጭት የተጎዳ ህብረተሰብ መልሶ ወደ ሰላም ለማምጣትና የተረጋጋ ሕይወት ይመሩ ዘንድ የአስታራቂነት ድርሻ አላቸዉ እነዚህ ሠላምና እርቅን የሚያወርዱ ተsማት የጉማ፤የከለቻ፤ጫጩ፤ሲንቄ፤ ቦኩ፤ ሽምግልና፤ የመሳሰሉት ናቸዉ ፡፡ ከነዚህም መካከል እስት የሲንቄ ተsም ደንብና ሥርዓት እንመልከት፡፡

ሲንቄ
#ሲንቄ$ ግጭቶች አለመግባባቶችን ባሉበት ሥፍራዎች እነደ ቦኩ ሁሉ ያላንዳች ሥጋት በጠቡ መካከል በመግባት እኩይ ድርጊቱን እንዳይፈፀም ተገን በመሆን ግጭቱን እንዲበርድ ወይንም እንዲቆም ያደርጋል፡፡ ከነዚህ ባሻገር ሲንቄ ሰላምና መረጋጋት ይሰፈን ዘንድ ሴቶችን በማደራጀት በኩል ትልቅ ሥፍራ አለዉ፡፡
ከሽማግሌዎች ባሻገር የተጋደሉት፡ ክፍሎች ካሉ ሴቶች #ሲንቄ$ አቸዉን ይዘዉ ወዳንድ ታዋቂ መድረክ በመሰባሰብ ለእርቀ ሰላሙ መዉረድ ልመናቸዉን ያቀርባሉ፡

Categories: Uncategorized

0 Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published.